Posted News

Recent News

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ አመት ስራ ግምገማ እና ለባለሞያዎቹ ዕዉቅና ሰጠ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ 2018 በጀት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ገምግሟል ። በስራ ቡድኖች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ አፈፃፀም መመዝገቡም ተመላክቷል ። የቀጣይ ጊዚያት ተግባራትን እና የማስፈፀሚያ ስልቶችም ለውይይት የቀረቡ ሲሆን የመምሪየው ሀላፊ አቶ ደምሰው መንበሩ ከዚህ የበለጠ ለመስራት ሁሉም ፈፃሚ በየስራ ድርሻው የተቀመጠውን የቁልፍ ነጥቦች መለኪያን መሠረት አድርገን መስራት ይገባል ብለዋል ። ከዚህ በተጨማሪ የዞኑን በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም የነበራቸውለመምሪያው ባለሙያዎች ማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና ሰርተፊኬት ፣ የማኔጅመንት አባላት የዕውቅና ምስክር ወረቀት ከመምሪያው ሀላፊ ከአቶ ደምሰው መንበሩ እጅ ተቀብለዋል ።

በአብክመ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለዞናችን የመስክ ድጋፍ ተደረገ

በአብክመ የኢንዱሰትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ድጋፍ ቡድን በሰሜ ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ እና በስሩ ለሚገኙት ቡልጋ ከተማ አስተዳደር እና አንጎለላና ጣራ ወረዳ በመስክ እና በቢሮ በመገኘት ድጋፍ ሰጥቷል ። በዚህ ድጋፍ የዞኑን መምሪያ ወረዳዎችን የሚደግፍበትን እና በአጠቃላይ የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን ፤ የዞኑን የቁልፍና አበይት ተግብራት አፈፃፀምን በ2018 አሰከ አሁን ባለው የሰራ እንቅስቃሴ  የነበሩ ጠንካራና እና ደካማ ስራዎችን ያመላከቱ ሲሆን በመጨረሻም ሁለተኛው ሩብ አመት አፈፃፀሙ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ   የቀጣይ አቅጣጫዎችን በመስቀመጥ  ለመግባባት ተችሏል ።

Leave a Comment:
Looking for Professional Approach and Quality Services?