የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ አመት ስራ ግምገማ እና ለባለሞያዎቹ ዕዉቅና ሰጠ፡፡
Office news quarter evaluation Posted by nszii on 2026-01-23 17:05:34 |
የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ 2018 በጀት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ገምግሟል ። በስራ ቡድኖች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ አፈፃፀም መመዝገቡም ተመላክቷል ። የቀጣይ ጊዚያት ተግባራትን እና የማስፈፀሚያ ስልቶችም ለውይይት የቀረቡ ሲሆን የመምሪየው ሀላፊ አቶ ደምሰው መንበሩ ከዚህ የበለጠ ለመስራት ሁሉም ፈፃሚ በየስራ ድርሻው የተቀመጠውን የቁልፍ ነጥቦች መለኪያን መሠረት አድርገን መስራት ይገባል ብለዋል ። ከዚህ በተጨማሪ የዞኑን በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም የነበራቸውለመምሪያው ባለሙያዎች ማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና ሰርተፊኬት ፣ የማኔጅመንት አባላት የዕውቅና ምስክር ወረቀት ከመምሪያው ሀላፊ ከአቶ ደምሰው መንበሩ እጅ ተቀብለዋል ።
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 27