የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ
Events
Ethiopian Tamirit
Posted by nszii on 2025-08-10 14:37:56 |
Last Updated by nszii on 2025-08-10 14:37:56
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ስትሪንግ ኮሚቴ እቅዱን እና ተግባራቶችን ገመገመ።
በሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የኢንቨስትመንቱን ዘርፍ የሚያነቃቃውን የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ሁነት የካቲት 2/2017 ዓ.ም በዞኑ አንጎለላና ጠራ ወረዳ ማካሄዱን ተከትሎ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
በዛሬው እለትም ሁሉም የዞን መምሪያ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ግምገማ ተደርጓል።
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ እና የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አይነኩሉ አበበ መድረኩን መርተውታል።
የመምሪያው ሃላፊ አቶ ደምሰው መንበሩ መነሻ ሃሳብ አቅርበዋል ውይይትም ተደርጎበታል። የቀጣይ አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል
- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ተቋማዊ ሆኖ እንዲመራ ማድረግ እንዳለበት
- 5ቱ የክላስተር አስተባባሪዎች በስራቸው ያሉትን ኮሚቴዎች እቅድ አቅደው እንዲወያዩ አቅጣጫ ተቀምጧል
- የኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ መድረኩን በድምቀት ለማክበር ሁሉም የክላስተር አስተባባሪ በባለቤትነት በመያዝ በአሉን በድምቀት ለማክበር የድርሻውን መወጣት እንዳለበት መግባባት ተፈጥሯል።
በየደረጃ ያለ አመራር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ላይ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ የተጠናከረ ስራ መሰራት እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል።
Share: Facebook |
Twitter |
Whatsapp |
Linkedin Visits: 86