Posted News

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ

Events Ethiopian Tamirit

Posted by nszii on 2025-08-10 14:37:55 | የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የባለሃብት ምክክር መድረክ /የኢንቨስትመንት ፎረም/ በአንጎለላናጣራ ወረዳ ጎልባ ቀበሌ የካቲት 2/2017 ዓም ተካሂዷል፡፡ በዚህ መድረክ ላይ የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣ የወረዳ አመራሮች ፣ አጋር አካላት ፣ ባለሃብቶች ፣ የዞን መምሪያ ማኔጅመንት አባላት እና ባለሞያዎች ተገኝዋል፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አብዱ ሁሴን (ዶክተር)በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ጎለባ ቀበሌ የሚገኘውን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ባጃጆችን የሚያመርት እና የወረቀት ፋብሪካዎችን መርቀዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አህመድን መሃመድ (ዶክተር)፣ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዲሪስ አብዱን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
አመራሮቹ ከምርቃ ሥነ ሥርዓቱ በተጓዳኝ ሌሎች በአንጎለላና ጠራ እና ቡልጋ ከተማ አስተዳደር በማምረት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎችን በመጎብኘት አበረታተዋል።
ከተጎበኙት ፋብሪካዎች መካከል በአንጎለላና ጠራ ወረዳ የሚገኘው ጀር የተቀናጀ የምግብ ማምረቻ፣ ኤቨርብራት የፕላስቲክ ፋብሪካ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ጀር የተቀናጀ የምግብ ማምረቻ በአሁኑ ሰዓት ዘይት እያመረተ ሲሆን፣ በቀጣይ ሁለት ወራት አልሚ ምግቦችን ማምረት እንደሚጀምር ተጠቁሟል።
በተዘጋጀው መድረክ ላይ የዞኑን የኢንቨስትመንት ሰነድ በዞኑ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ደምሰው መንበሩ የቀረበ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ፓነል ውይይት ተደርጓል፡፡ በፓናል ውይይቱ ላይ በባለሃብቱ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ይተሰጣቸው ሲሆኑ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ምላሸ የሚሰጣቸውም እንዳሉ ተገልጧል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ግንባታቸውን ጨርሰው ወደ ምርት ለገቡ 10 የአምራች ኢንዱስትሪዎች የሰርተፊኬት እና የክሪሰታል ሽልማት ከክብር እንግዶቹ ተቀብለዋል፡፡ለአጋር አካላትም እንዲሁ ስለነበራቸው መልካም አስተዋጽዖ የሰረተፊኬት ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 81


Leave a Comment:
Looking for Professional Approach and Quality Services?