Posted News

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ አመት ስራ ግምገማ እና ለባለሞያዎቹ ዕዉቅና ሰጠ፡፡

Office news quarter evaluation

Posted by nszii on 2025-10-31 04:31:17 | የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት  አንደኛ ሩብ አመት ስራ ግምገማ እና ለባለሞያዎቹ ዕዉቅና ሰጠ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ 2018 በጀት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ገምግሟል ። በስራ ቡድኖች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ አፈፃፀም መመዝገቡም ተመላክቷል ። የቀጣይ ጊዚያት ተግባራትን እና የማስፈፀሚያ ስልቶችም ለውይይት የቀረቡ ሲሆን የመምሪየው ሀላፊ አቶ ደምሰው መንበሩ ከዚህ የበለጠ ለመስራት ሁሉም ፈፃሚ በየስራ ድርሻው የተቀመጠውን የቁልፍ ነጥቦች መለኪያን መሠረት አድርገን መስራት ይገባል ብለዋል ። ከዚህ በተጨማሪ የዞኑን በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም የነበራቸውለመምሪያው ባለሙያዎች ማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና ሰርተፊኬት ፣ የማኔጅመንት አባላት የዕውቅና ምስክር ወረቀት ከመምሪያው ሀላፊ ከአቶ ደምሰው መንበሩ እጅ ተቀብለዋል ።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 12


Leave a Comment:
Looking for Professional Approach and Quality Services?