የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስተሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ከሃምሌ 23 /2017 ዓም ጅምሮ በቡልጋ ከተማ አስተዳደር የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምልከታ እና ለከተማው እንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ሱፕርቪዝን ድጋፍ አድርጓል፡፡
Manufacturing Sectors Agro-prcossingPosted by nszii on 2025-10-31 04:54:03 | Last Updated by nszii on 2025-10-31 04:54:03
 
  
              ቀን 09/12/2017
የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የመስክ መልስ ግምገማውን አደረገ።
ዞኑ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሆነ ውሎ አድሯል ቡልጋ ከተማ አሰተዳደርም ለኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ምቹ እና የኢንቨስትመንት ማዳረሻ እየሆነ መጥቷል። ለዚህም ማሳያው ከለሚ ናሽናል ሴመንት ቀጥሎ ትልቁ የባይጅ ሴራሚክ ፋብሪካ ግንባታው በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ እና የመስሪያ ሸዱ በ86,000 ካሜ ላይ አርፎ እየተጠናቀቀ ይገኛል። በቡልጋ ከተማ አስተዳደር ከሐምሌ 25- ነሐሴ 5/2017 የቆየ 8አባላት የያዘ ጠንካራ የባለሙያ ስምሪት በመስጠት 168 ፕሮጀክቶችን በር ከበር በመንቀሳቀስ እንድታዪ ሲደረግ ይኸም ለዞናችንም ሆነ ለክልላቸን ተሞክሮ የሚሆኑ ግኝቶችተገኝተዋል ከማምረት አቅም መሻሻል:የስራ እድሎችን መፍጠሪያ ሀብት ከማስፋት:ከመመሪያ እና ደንቦች መከበር:የአምራች ኢንዱስትሪን ከመከታተል: እንድሁም የክላስተር አደረጃጀቶ ጋር መልካም ጅምሮችና የባለሀብቱን የስራ ተነሻሻነት በመጨመር ዞናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ምቹና ተመራጭ እየሆነ እንደመጣ ያሳያል። በአንፃሩ በአንዳንድ አልሚዎችና ባለሀብቶች ደግሞ ችግሮች እንዳሉ ማግኘት የተቻለ ሲሆን የተረከቡትን ቦታ ያለስራ አጥሮ መቀመጥ:ግንባታ ጀምሮ ማቆም :ሞርት ማምረት ጀምሮ ማቆሙ: የመብራት የመንገድ እና የቴሌ የፋይናንስ መሰል ችግሮች መኖራቸውን አስተውለናል።
በሌላው በኩል በ2016እና 2017 መሬት የወሰዱ ባለሀብቶች የተሻለ የግንባታ ሂደት ላይ መኖራቸው ብቻ ሳይሆን የባለሀብቶቻችንና የመንግስት ፍላጎት ምን ያህል እየተጣጣመ መምጣቱን የሚሳይና የሚበረታታ ተግባር ነው።
በአጠቃለይ ለ2018 ዕቅድ ላይ የታዪ ምልከታዎችን በማካተት አሁንም የክልሉ እንዲሁም ሀገራዊ የኢንቨስትመን መዳረሻነታችንን አጠናክርን እንድቀጥል እና አምራች ኢንዱስትሪው እንድነቃቃ ትልቅ ግብአት ከማግኘታችን ባለፈ የነበሩ አንዳንድ ችግሮችን እንድናርም በር የከፈተልን ስምሪት እንደነበር መወሰድ ይቻላል።
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 40